ጋዛ የ 1.5 ሚልዮን ኅዝብ እስር ቤት
እስራኤል በ2006 የካቲት ዉስጥ ፍልስጤም ባደረገዉ ምርጯ ማግስት፣ጋዛ ላይ የማያቋርጥ የፖለቲካ ና ኢኮኖሚ ማዕቀብ ጀመረ። ከ2007 በኋላ ዕቀባዉ ጠነከረ። ጋዛ ከአየር ከምድር እንዲሁም ከበሃር ታገደ። ሰዉ ና የንግድ እቃዎችን ማስወጣት ማስገባት ዉስን ሆነ። ከታህሳስ 2008 እስከ ጥር 2009 ድረስ ለ22 ቀን ባደረገችዉ ዘግናኝ ኦፕረይሽን፤ለመኖር መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች የደረቀበት ጋዛ የእርሻ ቦታዎች፥የስራ ቦታዎች፥የመኖሪያ ቤቶች ና ትምህርት ቤቶች ወደመዋል። እስካሁን ድረስ ጋዛ ዉስጥ 1.5 ሚልዮን ፍልስጤም የቁም እስረኛ ሆኗል። ለመኖር ትግላቸዉን ቀጥለዋል። የጋዛ ህዝብ 72%ቱ በርሃብ ይሰቃያል፤ከዚህም 65%ቱ ህጻናት ናቸዉ፤ከህጻናቱም 10%ቱ የአካል ጉዳተኞች ናቸዉ። የተባበሩት መንግስታት ይህንን ሁኔታ ሊቋቋሙት የማይችሉት መሆኑን ገልጿል።


የአለማችን ህሊና በዚህ ጉዞ ተገናኘ
በ2010 ግንቦት ላይ 6 ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች፦İHH፣Free Gazza Movemenet፣European Campaign to End the Siege on Gaza፣Ship to gazza፣Greece Ship to gazza፣Sweden እና The International committee to Lift the Seige on Gazza በአጠቃላይ በግምት ወደ 6000 ቶን እርዳታ ጋዛ ለማድረስ ጉዞ ተደርጓል። በጉዞዉ ላይ 750 አክቲቪስቶች ነበሩ። ከጀርመን፥ኩዌት፥እስራዔል አየርላንድ፥ሲዊዘርላንድ፥ግሪክ ሰሜን ቆጵሮስ፥ሞሮኮ፥የመን፥ግብጽ ና አልጀሪያ የመሳሰሉት ከ37 አገሮች የመጡ ሲሆን ከእነርሱም መካከል ከ15 በላይ የህዝብ ተዎካይ ከ60 በላይ አለምአቀፍ ፕሬስ አባላት አርቲስቶች እና የሰላም ኖበል ተሸላሚ አክቲቪስቶች ይገኙ ነበር።


እስራዔል ሲቪሎችን ደበደበች
ግንቦት 30 ስድስት  መርከብ፦Defne ፣ Gazze I፣ Eleftheri Mesogios፣Sfendoni፣Challenger I እንዲሁም mavi Marmara ቆጵሮስ አጠገብ ተገናኙ። ግንቦት 31 ጧት ወደ ጋዛ የሚሄደዉ ኮንቮይ የእስራዔል ጦር ሃይል የሆኑ ፈጣን የጦር መርከብ 3 ሄሊኮብተር ፣2 ሰርጓጅ መርከብ እና በ30 ጀልባዎች ተከበቡ። ጧት 4:30 ገደማ ለጋዛ 73 ማይል ሲቀረዉ ዓለም ዓቀፍ የዉሃ ክልል ዉስጥ እስከ አፍንቺጯዉ የታጠቁ የእስራዔል ወታደሮች የመርከቦቹ  መሪ ማቪ ማርማራ ላይ እየተኮሱ ወጡበት።ወታደሮች ፕላስቲክ ና እዉነተኛ ጥይቶችን ተጠቅመዉ ምንም መሳሪያ የሌላቸዉን ሲቪሎችን አልመዉ ነበር። ስምንት ቱርክ፣አንድ ቱርክ ና አሜሪካዊ የሆነ በአጠቃላይ ዘጠኝ አክቲቪስቶች ተገደሉ፤ሃምሳ ስድስት ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደረሰባቸዉ። መርከቡ ጋ ይደረግ የነበረዉ ላይቭ ስርጭት ተቋረጠ ሆኖም ግን የእስራዔል ወታደረች ያልተገነዘቡት ሁለተኛዉ ጣቢያ ላይ ስርጭቱ ቀጠለ ከዚያም እንሰሳዊ የሆነ ድርጊቱን አለም ተመለከተ መሰከረ። አክቲቪስቶችን በሙሉ ከመርከቡ አስወረዱ፤እጆቻቸዉ የፍጥኝ ታሰሩ፤ምግብና ዉሃ ተከለከሉ፤መጸዳጃ ቤት እንዳይሄዱ ታቀቡ፤የግል ንብረቶቻቸዉን ተቀሙ። 750 አክቲቪስቶች ያለፍላጎት መያዛቸዉ ሳያንስ እስራኤል ያለ ፈቃድ በመግባት በሚል ሰበብ ታሰሩ። መርከቦቹ ቴልአቪቭ አጠገብ ወደሚገኘዉ አሽዶድ(ASHDOD) ወደብ ተወሰዱ።አክቲቪስቶች እያንዳንዳቸዉ በፖሊሶች ታጅበዉ ና እጆቻቸዉ በካቴና ታስረዉ ከመርከቡ ተወረዱ። መንገደኞችን በሙሉ አስወልቀዉ ደጋግመዉ ፈተሿቸዉ።እጅግ በጣም ጥብቅ በሆነ ቁጥጥር ዉስጥ ፎቶግራፎች፥ የጣት ና የአይን አሻራም ተወሰደ፤በተጨማሪም ቢርሸቫ(BEER-SHEVA) በተባለዉ አሰቃቂነቱ በታወቀዉ እስር ቤት ተከተቱ። እርስበርሳቸዉ መነጋገር እንዲሁም ስልክ መደወል ተከለከሉ።በከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ድርድር ና አለማቀፋዊ ጫና ምክንያት ከ2 ቀን በኋላ ነጻ ተለቀቁ። ግንቦት 31 ምሽት ማቪማርማራ ላይ የተፈጸመዉ ፍልስጤም ዉስጥ ከሚፈጸመዉ ኢ-ሰበዓዊ ድርጊት ጋር ምንም ልዩነት የለዉም።ለስነልቦናዊ ና አካላዊ ጉዳት መዳረግ፣መጠለፍ፣መታሰር፣መቁሰል፣በርሃብ መቀጣት፣መነጋገርን መከልከል፣መገደል...


ፍልስጤም ዉስጥ ሰዎች ለ 63 ዓመት እንደዚህ ይኖራሉ።